የዳግማዊ አፄ ምኒልክ የአስተዳደር፣ የሥልጣኔና የዐድዋ ድል ታሪክ በአሥር የተለያዩ አርዕስቶች ተከፋፍሎ የቀረበውን ትረካ በእያንዳንዱ አርዕስት ሥር የሚገኘውን የድምጽ ማጫወቻ በመጠቀም ትረካውን ማዳመጥ ይችላሉ | |
---|---|
ክፍል አንድ ትወልድ፣ ከመቅደላ መጥፋትና የግዛት አንድነትን ማስከበር |
ክፍል ሁለት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ የአመራር ጥበብና ዲፕሎማሲያዊ ብልሃት |
ክፍል ሶስት ፋሽስት ኢጣሊያ ከዓድዋ ጦርነት በፊት የመረብን ወንዝ ተሻግሮ እንዴት ሊገባ ቻለ? |
ክፍል አራት የሐማሴንና የትግራይ መኳንንቶች ክህደት፣የኤርትራ በኢጣሊያ መያዝና የውጫሌ ውል ያስከተለው መዘዝ |
ክፍል አምስት በዐድዋ ጦርነት ዋዜማ የኢጣሊያ ሰላዮች ፕሮፓጋንዳና ከፋፍሎ የመግዛት ሤራ |
ክፍል ስድስት የአምባላጌ ጦርነትና የመቀሌን ምሽግ ለማስለቀቅ የእቴጌ ጣይቱ የጦር አመራር ብልሀት |
ክፍል ሰባት በዐድዋ ጦርነት የፋሽስት ኢጣሊያ ጦር እና የኢትዮጵያ ሠራዊት አሠላለፍ፣ የዐድዋ ጦርነት መጀመር |
ክፍል ስምንት ስለዐድዋ ጦርነት በኢትዮጵያ የታሪክ ጸሐፍያን ዕይታ፣ ከድሉ በኋላ የኤርትራ ጉዳይና የዐድዋ ድል ገፅታ በዓለም አደባባይ |
ክፍል ዘጠኝ ከዐድዋ ድል በኋላ የተከናወኑ ሁኔታዎችና በዐድዋ ጦርነት ስለተማረኩ የኢጣሊያ ወታደሮች አያያዝ |
የመጨረሻ ክፍል የዳግማዊ አፄ ምኒልክ የግል ባሕርያት፣ ልዩ ልዩ ችሎታዎች፣ የምኒልክ መታመምና ሕልፈተ ሕይዎት |
"መራራ እውነት በኢትዮጵያ ታሪክ" ደራሲ፡- ታዬ ቦጋለ አረጋ፤ ሰኔ 2011 ዓ.ም.
የኢጣሊያ መንግሥት አሰብን ለመግዛት ለምን ፈለገ?
ይህ ወቅት፤ ፋሽስቶች ለመውደቅ የሚንገዳገደውን የኢጣሊያ መንግሥት በእግሩ ካቆሙ በኋላ አገራቸውን ወደ ጥንቱ የሮማውያን አገዛዝ ለመመለስ ሲሉ የቅኝ ግዛት አገር የሚፈልጉበት ወቀት ነበር፡፡ በሜድትራንያን ባህር በኩል የሚዋሰኑ አገሮችን በቅኝ ግዛትነት ለመያዝ አስበው ነበር፡፡ ግን፤ ፈረንሳዮች አስቀድመው አልጀሪያንና ቱኒዚያን ይዘው ስለነበር፤ ጣሊያኖች ሞሮኮን ለመያዝ ቢያስቡም የሞሮኮው ሱልጣን የማይበገር ሀያል ሆነባቸው፡፡ ጣሊያኖች ተስፋ ሳይቆርጡ በሌላ አቅጣጫ በቀይ ባሕርና በሕንድ ውቅያኖስ በኩል የቅኝ ግዛት አገር ሲያፈላልጉ ሳለ፤ በድንገት በኢጣሊያ ፓርላማ፤ “ቀይ ባሕር ለሜድትራንያን ቁልፍ ነው፡፡” በሚል መፈክር ተሞላ፡፡ በዚህን ጊዜ ነው የኢጣሊያ መንግሥት በአባ ጁሴፔ አማካኝነት የተገኘውን የመርከብ ኩባንያ ገዝቶ ሰኔ 19 ቀን 1874 ዓ.ም. አሰብ የኢጣሊያ መንግሥት ግዛት መሆኑን ያወጀው፡፡የኢጣሊያ መንግሥት የምፅዋን ወደብ መቆጣጠርና የኢትዮጵያ ምላሽ
በዚያን ዘመን አፍሪካ በአብዛኛው በግልፅም ሆነ በስውር በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር ነበረች ማለት ይቻላል፡፡ በወቅቱም እንግሊዞች ከታላላቅ ኃይሎች ጋር የገጠማቸውን ትልቅ የፖለቲካ ሽኩቻ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም፤ በሌሎች ኃያላን ዘንድ በንቀት ይታይ የነበረው የኢጣሊያ መንግሥት አንድ የወታደር ኃይል ወደ ምፅዋ እንዲልክና ሱዳን ውስጥ እንግሊዝን የሚበጠብጠውን የመሀዲስት ኃይሎች ለመቆጣጠር እንደሚቻል በማሰብ፤ ምፅዋን የያዙትን ግብፆችን አስወጥተው በምትኩ የኢጣሊያ መንግሥት ቦታውን እንዲረከብ የሚያስችል ውል እንግሊዞች ከኢጣሊያ ጋር ተፈራረሙ፡፡ በውሉም መሰረት በሚስጥር የተላከው የኢጣሊያ የወታደር ቡድን ጥር 28 ቀን 1877 ዓ.ም. ጧት ምፅዋ ገባ፡፡ አፄ ዮሐንስ እንግሊዞች ምፅዋን ያለእርሳቸው እውቅና ለኢጣሊያ መንግሥት አሳልፈው የመስጠታቸው ጉዳይ ግር ቢላቸውም፤ ጉዳዩን በማጣራት ላይ እንዳሉ የኢጣሊያ መንግሥት በምፅዋም ሆነ በአሰብ ወደብ ምንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ከለከለ፡፡ ዳግማዊ አፄ ምኒልክም ለኢጣሊያው ንጉሠ ነገሥት ደብዳቤ በመጻፍ የኢጣሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ጋር ጦርነት ለመግጠም አስቦ ምፅዋ መግባቱን በመስማታቸው ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ ምፅዋም የጣሊያኖች የጦር መሣሪያ ማከማቻ መሆን ቀጠለ፡፡ ምፅዋ በኢጣሊያኖች መያዙን የሰሙት አፄ ዮሐንስም 159 ሺህ ጦር አሰልፈው ጣሊያኖችን ለመውጋት ዘምተው ቢጠባበቁም፤ የጣሊያን ወታደሮች 50 ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው በመግባት ሰሓጢ በተባለው ስፍራ መሽገው አልንቀሳቀስ አሏቸው፡፡ የአፄ ዮሐንስ ጦር ሁለት ወራት ሙሉ በመቆየቱ ስንቁን ጨርሷል፡፡ የደጋው ወታደር የቆላውን ሙቀት መቋቋም አልቻለም፡፡ የሱዳኑ የመሀዲስት ጦርም በጎንደር በኩል ገብቶ እየተዋጋ ድል እየቀናው ነው፡፡ በዚህ ምክንያት አፄ ዮሐንስ ወደ ደጋው ተጉዘው አሥመራ ከደረሱ በኋላ፤ የመረብ ምላሽ ገዥና የጦር አዛዥ የነበሩትን ራስ አሉላን ከሥልጣናቸው ሽረው ከአስመራ ተመለሱ፡፡