Content-Language: am ጥያቄና መልስ ገጽ ሁለት
header image




ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ማጫወቻ በመጠቀም
20 ጥያቄዎችን ለመመለስ ይሞክሩ
ለእያንዳንዱ ጥያቄ 5 ሰከንድ ተሰቷል
ከ 5 ሰከንድ በኋላ መልሱ ይሰጣል















የሚያውቁትን ለማስታወስ እንዲረዳዎት ሳጥኑ ውስጥ ያሉትን ቀላል ጥያቄዎች አንብበው ለመመለስ ይሞክሩ የጥያቄውን መልስ ሳጥኑን በመጫን ያገኙታል


የተጫኑትን የጥያቄ ሳጥን ወደ ቀድሞው ቦታ ለመመለስ በድጋሚ ሳጥኑን ይጫኑት


ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት
( ስለ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ)

1. በዐድዋ ጦርነት የገጠመውን ሀፍረት ለመሻር እና፣
2. እጅግ ለምና በከርሰ ምድር ሐብቷ የበለፀገችውን ኢትየጵያን ለመቆጣጠር ነበር፡፡

እንግሊዝ

መስከረም 22 ቀን 1928 ዓ.ም.

ደጃዝማች ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ ይባላል፡፡

Haile Selassie Gugsa

ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ፤ ከአፄ ዮሐንስ የልጅ ልጅ የሚወለድ ሲሆን ባለቤቱም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ልጅ ልዕልት ዘነበወርቅ ነበሩ፡፡
ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ በተሰጠው ማዕረግ ደስተኛ ስላልነበረ ቂም መቋጠሩን የተረዱት የኢጣሊያ አዛዦችም ከራስ ስዩም መንገሻ ነጥቀን ሙሉ ትግራይን እንሰጥሀለን ብለውት ስለነበረ ይህን ተሰፋ አድርጎ ከጠላት ጋር ወግኖ አገሩን ሲወጋ ቆይቶ በኋላም ጣሊያኖች የተመኘውን የራስነት ማዕረግ ብቻ ሰተውት ነበር፡፡
ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ለቀው ከወጡ በኋላ ግን በአገር ክህደት ወንጀል ተከሶና የተሠጠውም የራስነት ማዕረግ ተገፎ ለብዙ ዘመናት በእስር ቤት ከቆየ በኋላ ሕይወቱ አልፏል፡፡

12 ሚሊዮን

ዶክተር መላኩ በያን ይባላል፡፡
Dr. Melaku Beyan
ዶክተር መላኩ በያን የተወለደው በወሎ ጠቅላይ ግዛት ሲሆን በ30 ዓመት እድሜው ወደ አሜሪካ ለትምህርት ተልኮ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ዝነኛና ታዋቂ ከሆነው አፍሪካ አሜሪካዉያን ከሚማሩበት ከሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ የተመረቀ ብቸኛውና የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሕክምና ዶክተር ነበር፡፡
ዶክተር መላኩ፤ በአሜሪካ ምድር “የኢትዮጵያ የዓለም ፌደሬሽን” የተሰኘውን ድርጅት በኒውዮርክ ከተማ ነሐሴ 19 ቀን 1929 ዓ. ም. በመመስረት ታላቅ ተግባር የፈፀመ እውቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር ነበር፡፡

( ስለ ዶክተር መላኩ በያን የበለጠ ለማንበብ) ይህን ሊንክ ተጭነው ክፍል 19ን ያንብቡ

ኢምፔሪያል ኢትዮጵያ አቪየሽን (Ethiopian Imperial Aviation)

ኮሎኔል ስምረት መድኃኔ ይባላሉ፡
Col. Semeret Medehane
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታህሳስ 12 ቀን 1938 ዓ. ም. ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በአሜሪካኖች ይመራ ነበር፡፡
ከ26 ዓመታት ቆይታ በኋላ፣ በ1964 ዓ. ም. ኮሎኔል ስምረት መድኃኔ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ፡፡
የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አባት ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ይባላሉ::
(ስለ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ)
Ras Mekonnen Wolde Michael
ቀዳማዊ ምኒልከ
Kedamawi Menilk
በአክሱሙ ንቡረዕድ ይስሐቅ በ14ኛው ክፍለ ዘመን በግዝ ቋንቋ በተጻፈው ክብረ ነገሥት ላይ እንደተመዘገበው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ንጉሥ ቀዳማዊ ምኒልክ ከንጉሥ ሰለሞንና ከንግሥተ ሳባ የተወለደ ነው፡፡
ንጉሥ ሰለሞን የቃል ኪዳኑን ታቦት ለልጁ ለምኒልክ በስጦታ ከሰጠው በኋላ ምኒልክ በርካታ እስራኤላውያንን አስከትሎ ወደ ሀገሩ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ እናቱ ንግሥት ሳባ ስትሞት በአንድ ሺህ ዓመተ ዓለም ዘውዱን ደፍቶ ቀዳማዊ ምኒልክ ተብሎ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ንጉሥ መሆን ቻለ፡፡
ቀዳማዊ ምኒልክ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከሆነ በኋላ “የመጀመሪያውን ሰለሞናዊ ሥርዎ መንግሥት” (Solomonic Dynasty) መሠረተ፡፡
ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ ለ 3ሺህ ዘመናት የቆየው ሰለሞናዊው ሥርዎ መንግሥት፤ ደርግ በ1966 ዓ. ም. በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ሲረከብ፤ 225ኛው የሰለሞናዊው ስርዎ መንግሥት የመጨረሻ ፍጻሜው ሆነ፡፡

(ስለ ዳግማዊ ምኒልክ የበለጠ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ) ዳግማዊ ምኒልክ

(ስለ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበለጠ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ) ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
የክብር ዶክተር ስንዱ ገብሩ ይባላሉ፡፡
Dr. Senedu Gebru
ዶክተር ስንዱ፤ በውጥጭ አገር ትምህርት የቀሰሙ ሲሆን የታሪክ፣ የእንግሊዝኛና የፈረንሳይኛ ቋንቋዎችን ተምረዋል፡፡
የስንዱ ገብሩ ወላጅ አባት ከንቲባ ገብሩ፤ ታዋቂ ዲፕሎማት፣ የመጀመሪያው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝደንት፤ ኢጣሊያ ከኢትዮጵያ ለቃ ከወጣችም በኋላ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዝደንት፤ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥትም የመጀመሪያው የጎንደር አስተዳዳሪ ሆነው ያገለገሉ ናቸው፡፡
የከንቲባ ገብሩ ታናሽ እህት የውብዳር ገብሩ ይባላሉ፡፡ የውብዳር ገብሩ፣ ከመነኮሱ በኋላ እማሆይ ጽጌ ማሪያም ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ይባላሉ፡፡
Tessema Eshete
ሐምሌ 20 ቀን 1869 ዓ. ም. ምንጃር የተወለዱት ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ፤ ከዓድዋ ድል በኋላ በሁለተኛው ዓመት ጀርመን አገር ተልከው የመጀመሪያ የሆነውን መዲናና ዘለሰኛ የያዘ የአማርኛ ዜማ በሸክላ ከአስቀረፁ በኋላ ሸክላውን ያስቀረፀው ኩባንያ የድካምዎ ዋጋ ይሁንዎ ብሎ የሰጣቸውን 16 ሺህ የጀርመን ፍራንክ ተቀብለው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ የብዙ ሙያዎች ባለቤት በመሆናቸው፤ ገጣሚ፣ ጥበበኛ፣ ሰዓሊ፣ ቀራፂ፣ የፖለቲካ ሹም፣ አሳሽና የተዋጣለት ፎቶግራፍ አንሺ እንደነበሩ ተዘግቧል፡፡ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ልጅ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሠማ፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ ለ27 ዓመታት የተጫወቱ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን ከአቋቋሙት ውስጥ አንዱ የሆኑ፣ የእግር ኳስን ሕግ ወደ አማርኛ የተረጎሙ፤ የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የፊፋ አባል የነበሩና በመጨረሻም የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት የነበሩ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያና ብሎም የአፍሪካ የዘመናዊ ስፖርት አባት የተባሉት አቶ ይድነቃቸው ተሠማ ነሐሴ 14 ቀን 1979 ዓ. ም. በተወለዱ በ66 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በ 1900 ዓ. ም. ካሳተሙት የሙዚቃ ሸክላ የተወሰደውን የ 1 ደቂቃ መዲናና ዘለሰኛ ሙዚቃ ቀጥለው ያዳምጡ፡፡

( ምስጋና ለ፤   Oscar Huerta Plaza)
እማሆይ ፅጌ ማሪያም ገብሩ ይባላሉ፡፡
Emahoy Tsigemariam
እማሆይ ፅጌ ማርያም ገብሩ፣ የጎንደር ከንቲባ ከነበሩት ከአባታቸው ከከንቲባ ገብሩ ደስታ በአዲስ አበባ ከተማ ታህሳስ 2 ቀን 1916 ዓ.ም. ተወለዱ።
ትምህርታቸውንም ስዊዘርላንድ ውስጥ በሚገኘው ቅዱስ ክርስትና (St. Christian) ውስጥ የሰብዓዊ ትምህርትን (Humanities) አጥንተዋል። እማሆይ ፅጌ ማሪያም ከመመንኮሳቸው በፊት የውብዳር ገብሩ ይባሉ ነበር፡፡ የዶክተር ስንዱ ገብሩ እህት ናቸው፡፡
ገና በ19 ዓመት ለጋ እድሜያቸው ከቤተሰቦቻቸው ጠፍተው ወደ ግሸን ማርያም በመሄድ ምንኩስና ተቀብለዋል፡፡
እየሩሳሌምም ለ30 ዓመታት ያህል ኖረዋል፡፡
ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ ከመላ ቤተሰባቸው ጋር በመሰደድ የጥቁር አንበሳ ጦር ተቀላቅለው በሽምቅ ውጊያ ሦስት ወንድሞቻቸው ተገድለዋል። ጦርነቱም ሲፋፋም ቤተሰባቸው በሙሉ ወደ ኔፕልስ፣ ጣሊያን በግዞት ተወሰዱ። በእስር ቆይታቸው አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ከካቶሊክ መነኮሳት ጋር በመሆኑ በውስጣቸው መንፈሳዊ ሕይወት እንዲያቆጠቁጥ ምክንያት ሆነ።
በ1998 ዓ. ም. ፍራንሲሊስ ፋልሴቶ የተባለው ፈረንሳዊ የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃዎችን ሰብስቦ እንደ አዲስ «ኢቶፒክስ» የተባለ ሲዲ ባሳተመበት ጊዜ ቁጥር 21 ላይ እማሆይ ፅጌ ማርያም ሥራዎችን አካቷል። ሲዲው በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለው ሰፊ ስርጭት አንፃር ስለ እማሆይ ፅጌ ማርያም ቀሪው ዓለም ብዙ እንዲያውቅ ረድቷል።
የተለያዩ የሙዚቃ ስራዎቻቸውንም በተለያዩ ኮንሰርቶች ላይ በማቅረብ የሚገኘውንም ገንዘብ ለድሆች መርጃ አውለዋል።
እማሆይ ፅጌማሪያም ገብሩ በተወለዱ በ99 ዓመታቸው መጋቢት 17 ቀን 1915 ዓ.ም. እየሩሳሌም ውስጥ አረፉ፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም እየሩሳሌም በሚገኘው በኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ

በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ
( ስለ ዳግማዊ አፄ ምኒል የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ)

እቴጌ ጣይቱ ሆቴል
እቴጌ ጣይቱ ሆቴል፤ ከዓድዋ ድል ከ10 ዓመት በኋላ በ1998 ዓ. ም. አሁን ፒያሣ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከተሠራ በኋላ እቴጌ ጣይቱ ራሳቸው እያሰተናገዱና በነፃም እየጋበዙ ተጋባዥ እንግዶችን የሆቴል አገልግሎት እንዳለማመዱ ተዘግቧል፡፡
(ስለ እቴጌ ጣይቱ የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ) እቴጌ ጣይቱ

ጀነራል አለልቤርቶኒ ይባላል፡፡
Albertoni
በዓድዋ ጦርነት ወቅት ፋሽስት ኢጣሊያ ያሰለፈቻቸው ጀነራሎች ከዋናው አዛዥ ጋር አምስት ሲሆኑ ስማቸውም፤
1. ጀነራል ባራቲዬሪ - ዋና የጦር አዛዥ፣
2. ጀነራል አሪሞንዲን፣
3. ጀነራል ዳቦር ሜዳ፣
4. ጀነራል አለልቤርቶኒ እና
5. በወቅቱ አዲስ ሹመት አግኝቶ የነበረው ጀነራል ኤሌና ይባላሉ፡፡