Content-Language: am
ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ ዮሐንስ
ወደ ላይኛው ገጽ ይሂዱ
ቀዳሚ ገጽ ▼
የታሪክ ማስታዎሻዎች ▼
አፄ ቴዎድሮስ
አፄ ዮሐንስ 4ኛ
ዳግማዊ ምኒልክ
ንግሥት ጣይቱ
ንግሥት ዘዉዲቱ
ልጅ እያሱ
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ ▼
አርበኞች ገጽ አንድ
አርበኞች ገጽ ሁለት
ጥያቄና መልስ ▼
ጥያቄና መልስ ገጽ አንድ
ጥያቄና መልስ ገጽ ሁለት
ስለ ድረ ገፅ አዘጋጁ
ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ ዮሐንስ
የልዑል ራስ ስዩም መንገሻ ዮሐንስ የማይጨው ጦርነት የአርበኝነት ታሪክ
Your browser does not support the audio element.
1. ትውልድና የሕይዎት ጉዞ
ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ
ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ በጎጃም ጠቅላይ ግዛት ዝምብሪ በምትባል የአገው ምድር ከተማ ውስጥ ሰኔ 17 ቀን 1878 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ አባታቸው፤ የ
አፄ ዮሐንስ 4ኛ
ልጅና አልጋ ወራሻቸው የሆኑት ራስ መንገሻ ዮሐንስ ሲሆኑ፤ እናታቸው የትግራይ ምክትል ገዥ የነበሩት የራስ ወሌ ብጡል ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ይባላሉ፡፡ ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ፤ አፄ ዮሐንስ ከሞቱ በኋላ የዳግማዊ ምኒልክ ተቀናቃኝ ነበሩ፡፡ የልዑል ራስ ስዩም መንገሻ የመጀመሪያ ሚስታቸው የ
ወሎው ንጉሥ ሚካኤል
ልጅና የ
ልጅ ኢያሱ
እህት ወይዘሮ ተዋበች ናቸው፡፡ ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ ከወይዘሮ ተዋበች የልዑል አሰፋወሰን ኃይለ ሥላሴን ባለቤት የሆኑትን ልዕልት ወለተ እስራኤል ስዩምን ወልደዋል፡፡
2. የማይጨው ጦርነት
ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ ከወታደሮቻቸው ጋር
ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ በማይጨው ዘመቻ፤ በሰሜን ጦር ግንባር የትግራይ ጦር አዛዥ ሆነው ተሰልፈዋል፡፡ ንጉሠ ነገሥት
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
የጦር ማዘዣ ጣቢያቸውን ህዳር 20 ቀን 1928 ዓ.ም. ወደ ደሴ ካዛወሩ በኋላ በትግራይ የሰፈረውን የወራሪው የፋሽስት ኢጣሊያ አዲሱ የጦር አዛዥ ማርሻል ባዶሊዮ ያለውን ኃይል ለመገመት አስበው ታህሳስ 5 ቀን የኢትዮጵያ የሰሜን ግንባር የጦር ኃይሎች ተቀናጅተው ማጥቃት እንደዲጀምሩ ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡ የዚህ የማጥቃት ዋና ዓላማ፤ የትግራይን የተለያዩ ስፍራዎች የተቆጣጠረውን የፋሽስት ጦር በተለያየ አቅጣጫ ማለትም፤ በመሐል፣ በግራና በቀኝ አቅጣጫ በማጥቃትና ኃይሉን ለሁለት ከፍሎ በማዳካም፤ በተለይ በግራ አቅጣጫ ያለው የኢትዮጵያ ጦር ኤርትራን ለመቆጣጣር ዕቅድ ነበረው፡፡ በዚህም መሠረት በልዑል ራስ ስዩም መንገሻ የሚመራው 30 ሺህ ጦር ቀደም ሲል በጠላት እጅ ተይዛ የነበረችውን አቢ አዲን ለማስለቀቅ ታህሳስ 12 ቀን በከፈተው ጥቃት ጠላትን አሸንፎ መልሶ ተቆጣጥሯል፡፡ ይሁን እንጅ የጠላት አይሮፕላን ያለማቋረጥ የሚያዘንበው የሙስታርድ ጋስ ቦምብ እጅግ ብዙ የኢትዮጵያ ሠራዊት ስለጨረሰና ጦርነቱን በዚህ ሁኔታ መቀጠሉ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ፤ የሚዋጋበትን ሥፍራ ለቆ ወደኋላ በመመለስ ከ
ልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ
ጦር ጋር ሠራዊታቸውን ይዘው ወደ ኋላ በመመለስ ከንጉሠ ነገሥቱ ጦር ጋር ለመቀላቀል ተገደዱ፡፡
3. የልዑል ራስ ስዩም መንገሻ የመጨረሻ ፍጻሜ
በ1953 ዓ.ም. በተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ወቅት፤ የመፈንቅለ መንግሥት ጠንሳሾቹ የመንግሥት ልዑላንን፣ መሳፍንትን፣ መኳንንትን እና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጠርተው አሁን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሆነው በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ውስጥ አስረዋቸው ነበር፡፡ ከታሰሩትም ውስጥ ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ አንደኛው ስለነበሩ የታሰሩት በሙሉ ያለምንም ምህረት በጥይት ሲረሸኑ እርሳቸውም አብረው ተረሽነዋል፡፡ በመጨረሻም አስከሬናቸው ወደ አክሱም ተወስዶ በአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡
ወደ አርበኞች ገጽ 1 ይመለሱ «
ምንጭ፤
"የታሪክ ማስታወሻ" ደራሲ፡- ደጃዝማች ከበደ ተሰማ 1962 ዓ.ም.
"የኢትዮጵያ ታሪክ - ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ" ደራሲ፡- ተክለ ጻድቅ መኩሪያ 1961 ዓ.ም.
የትረካው አጃቢ ሙዚቃ፣ ዋሽንት - በአንሙት ክንዴ
ዩቲውብ