የአፍሪካው ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ
Photo credit to:
blackoutdoors
ዓለማየሁ ቴዎድሮስ፤ የአፄ ቴዎድሮስ እና በኋላም የአፄ ዮሐንስ 4ኛ መቀመጫ እና የጎንደር ዋና ከተማ በነበረችው በደብረ ታቦር ከተማ ሚያዝያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም. ተወለደ፡፡
አፄ ቴወድሮስ ከሞቱ በኋላ እናቱም ወይዘሮ ጥሩወረቅ አከታትለው ስለሞቱ ብቻውን ቀረ፡፡
ወይዘሮ ጥሩወርቅ የሰሜኑ ገዥ የነበሩት የደጃዝማች ውቤ ልጅ ናቸው፡፡
ይሁን እንጅ የአለማየሁ እናት ሊሞቱ አቅራቢያ ካፒቴን እስፒዲን አስጠርተውና እጁን ይዘው፤
“...ልጄ አባት የለውም፡፡ እኔም እናቱ ልሞት ነው፡፡ ዘመድ ስለሌለው አንተ ዘመድ ሁነው፡፡ አባት ስለሌለው አንተ አባት ሁነው፡፡ ያልኩህን ሁሉ እንደምታደርግ ቃል ግባልኝ፡፡ ሲሉኝ፣ 'የጠየቁኝን ሁሉ እፈጽማለሁ ብየ ማልኩላቸው'፡፡” በማለት አስፒዲ የተናገረውን ጽፏል፡፡
ካፒቴን እስፒዲ የልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ ሞግዚት እንዲሆን በእንግሊዝ ጦር መሪ በጀነራል ናፒየር የተመደበ የህንድ የጦር መኮንን ነበር፡፡
አፄ ቴዎድሮስ፤ እጃቸውን ለእንግሊዝ ወታደሮች ላለመስጠት ብለው ሽጉጣቸውን ጠጥተው በራሳቸው ላይ እርምጃ ከወሰዱ በኋላ የእንግሊዝ ወታደሮች የንጉሠ ነገሥቱን የአፄ ቴዎድሮስን ንብረቶች ዘርፈው ከመቅደላ ሲወስዱ ልዑል ዓለማየሁንም ከዘረፏቸው ንብረቶች ጋር አብረው ወደ እንግሊዝ አገር ወሰዱት፡፡

Photo credit to: blackoutdoors